የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ድልድል ይፋ ሆነ

የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ድልድል

መስከረም 5/2015 (ዋልታ) የአፍሪካ የወንዶች ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን የማጣርያ ውድድር የምድብ ድልድል ዛሬ ይፋ ሆነ፡፡

ውድድሩ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በመርኃ ግብሩ መሰረት በምድብ አንድ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ሶማሊያ እንዲሁም በምድብ ሁለት ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ቡርንዲ መመደባቸውን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW