ጠ/ሚ ዐቢይ ለከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ሹመት ሰጡ

ግንቦት 26/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ሹመቶችን ሰጡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል:-
1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን – የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ
2. ካሊድ አብዱራሂማን – በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል
3. ወንድሙ ሴታ – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
4. ሄኖስ ወርቁ – የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚከተሉት ሹመቶች እንዲጸድቁ ጠይቀዋል፡፡
1. መሰረት ዳምጤ – የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር
2. አበራ ታደሰ – የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር