ጠ/ሚ ዐቢይ በመንግስታቱ የአዳጊ አገራት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኳታር ዶሃ ገቡ

የካቲት 26/2015 (ዋልታ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአዳጊ አገራት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኳታር ዶሃ ገብተዋል።

አምስተኛው የመንግስታቱ የአዳጊ አገራት ጉባኤ በዝቅተኛ የእድገት ደረጃ ላይ በሚገኙ አገራት ላይ በማተኮር የሚካሄድ ነው።

ጉባኤው ዛሬ ጀምሮ ለቀናት የሚቆይ ሲሆን ለጉባኤውም የመንግስታቱ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝን ጨምሮ የሀገራት መሪዎች ዶሃ ገብተዋል።