በአርቲስት ዓሊ ቢራ ስም በቢሾፍቱ ከተማ አዲስ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ

የካቲት 25/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢሾፍቱ ከተማ ድሬ ጂቱ ቀበሌ በአርቲስት አሊ ቢራ ስም ‘’ዓሊ ቢራ ቅርንጫፍ’’ በይፋ ስራ አስጀመረ።

ቅርንጫፉን መርቀው የከፈቱት የቀድሞው አባ ጋዳ በየነ ሳምባቶ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ወጋየሁ ገብረማርያም ሲሆኑ ቅርንጫፉ በአሁኑ ትውልድ ይበልጥ እንዲታወቅና በመጪው ትውልድ እንዳይዘነጋ ታስቦ እንደተከፈተ ተገልጿል።

ባንኩ ለክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የህይወት ዘመን ትሩፋቶች የተዘጋጀ መታሰቢያ እንደሆነም ከባንኩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።