ጠ/ሚ ዐቢይ በአስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያን እያገዙ ለሚገኙ አፍሪካውያን ምስጋና አቀረቡ

ነሐሴ 13/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትርሩ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “በአስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያን እያገዛችሁ ለምትገኙ የአፍሪካ መሪዎች፤ ምሁራንና እንዲሁም መላው አፍሪካውያን ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡

አፍሪካ በህብረት ታሸንፋለችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢቲዮጵያ እያደረገች ባለችው ትግል ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን የምታሳዩት ህብረት የሚደነቅና ሲታወስ የሚኖር መሆኑን በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል፡