ጠ/ሚ ዐቢይ በ39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ናይሮቢ ገቡ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኬንያ መዲና ናይሮቢ ገብተዋል።

ዛሬ በሚጀመረው የመሪዎች አስቸኳይ ስብሰባ በጉባኤው መሪዎቹ በአካባቢው የሚከሰተውን ድርቅ ማሸነፍ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።