ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሠላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አደረጉ

ሠላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ

ጥር 26/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሠላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የሰላም ድርድሩ ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ግንኙነት ያደረጉት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሃላላ ኬላ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡