ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው

የካቲት 26/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል።

ግምገማው አራቱን የአስተዳደርና ፍትህ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን በተመለከተ በቀረቡ አፈፃፀሞች ላይ በማተኮር ተጀምሯል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሰል የግምገማ መድረኮች በመንግሥት ተቋማት የመፈፀም ባህልን ለማዳበር የጀመሯቸው መሆናቸው ይታወሳል።