ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በአቡዳቢ በመሰራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎበኙ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥር 9/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአቡዳቢ በመሰራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጎብኘታቸውን አስታውቀዋል።

17 ሺሕ 682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት መሰጠቱን ገልጸው ለዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናቸዋለሁ ብለዋል።

ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተክርስቲያንም እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል መገባቱንም ጠቁመዋል፡፡

ይሄንን መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትምህርቶች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ እኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምሀርት ይሆነናል ብለዋል።