ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ተወያዩ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና ሺ ጂንፒንግ

ጥቅምት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን በቻይና ታላቁ የህዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ ያነሱ ሲሆን በተለይም በአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች ማለጽም በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አይሲቲ፣ ማእድን ልማት እና ቱሪዝም ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሁለትዮሽ ውይይቱ ወቅት ፕሬዝዳንት ሺ በኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ሁነት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንኳን ደስ ያለዎ ብለዋቸዋል::

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት (All Weather Strategic Cooperation Partnership) ደረጃ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል ማረጋገጣቸውን ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡