ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ


መጋቢት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው “የዛሬው ውይይት ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ነበር” ብለዋል።

በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ያለን ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ፅኑ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዛሬው ውይይታችንም ይህንኑ የጋራ አላማ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ነው ሲሉም አክለዋል።