ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አደም ፋራህ ፣  ዐቢይ አሕመድ፣  ተመስገን ጥሩነህ

የካቲት 28/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት መዲናችን ከከተማ መስፋፋት ጋር የሚመጣ ፍላጎትን የሚያጎሉ ወሳኝ የሆኑ የእድገት እና የለውጥ ሂደት ውስጥ ትገኛለች ብለዋል።

የዛሬው አይነት ስብሰባዎች በሚታዩ ክፍተቶች የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ብሎም መልካም አጋጣሚዎችን ለመለየት እጅግ አስፈላጊ ነው ሲሉም አመልክተዋል።