ጠ/ሚ ዐቢይ  የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት ዕውን አድርገናል አሉ

የካቲት 5/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት ዕውን አድርገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ተገኝተው የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት አስጀምረዋል።

ይህን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለህዝባችን የተናገርነውን በተግባር ፈጽመን ዛሬ የኢትዮጵያን የስንዴ ኤክስፖርት ዕውን አድርገናል ብለዋል።

እኛ የምናልም፣ ያለምነውን የምንናገር፣ የተናገርነውን ቀን ከሌት የምንሰራ፣ የሰራነውን ደግሞ አጠናቀን የምናሳይ ስለመሆናችንም ማረጋገጫ ነው ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከውጭ የሚገባ ስንዴን አስቀርታ ወደ ውጭ ለመላክ አቅዳ ስትሰራ መቆየቷ ይታወቃል፡፡