ፓርቲው በደቡብ ጎንደር የማኒፌስቶ ትውውቅ እና የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ ነው

ሚያዝያ 21/2013 (ዋልታ) – ብልጽግና ፓርቲ በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ወረዳ የማኒፌስቶ ትውውቅና የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ ይገኛል፡፡

በጎዳና ላይ ቅስቀሳው ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘው ተሸገርን ጨምሮ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ፣ በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ተገኝተዋል።

“ፅንፈኝነት እና ጥላቻ የአማራ ህዝብ እሴት አይደለም”፣ “ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሆነው ብልፅግና ይቅደም”፣ “ብልፅግና የገጠሙንን ችግሮች ሁሉ መፍቻ መንገድ ነው”፣ “እኛ ብልፅግናዎች ሀገራችን ወደ ማትወርድበት ከፍታ ሳትወጣ ወደ ኋላ አንመለስም” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች እየተሰሙ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አገኘው ተሻገር በሰላማዊ ሰልፍ ለተሳተፉ አካላት መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎም ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል::