የስቅለት እና የትንሳኤ በዓላት ሲከበሩ እውነተኛ ንስሃ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ጉባዔው ገለጸ

ሚያዝያ 21/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ህዝበ ክርስቲያኑ የስቅለት እና የትንሳኤ በዓላትን ሲያከብር በሀገሪቷ ስላሉት ችግሮች ከልብ በመጸጸት እውነተኛ ንስሃ በማድረግ እና በጸሎት ወደ ፈጣሪ በመጠጋት ሊሆን እንደሚገባ ገለጸ፡፡

ጉባኤው ለዋልታ በላከው መግለጫ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳቸሁ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከመቼውም ግዜ በላይ አስጨናቂ በመሆኑ ህዝበ ክርስትያኑ ራሱን ለንስሃ እና ለይቅርታ ክፍት በማድረግ በዓሉን ሊያከብር እንደሚገባ ጉባኤው አሳስቧል፡፡

የትንሳኤ በአል ሲከበር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኞች በማሰብ ሊሆን እንደሚገባም ጉኤው ገልጿል፡፡

ጉባኤው ህዝበ ክርስትያኑ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን ሳይዘናጋ እንዲተገብርም ጥሪ አቅርቧል፡፡