ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከጀርመን አቻቸው ጋር ተወያዩ

መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከጀርመኑ አቻቸው ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸው በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝና፣ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።