125ኛውን የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት ተካሄደ

የካቲት 21/2013 (ዋልታ) – 125ኛውን የአድዋ ድል ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲግንባታ ማስተባበርያ ማዕከል ግንባታ አቶ መለስ አለሙ  እንዳሉት  አድዋ ላይ የተሰለፉት  አባቶች ደማቸውን ሰውተው ሀገር እንዳስረከቡ ሁሉ፣ ወጣቱም የአሸናፊነት ስነ ልቦና በመታጠቅ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማሳለፍ ይጠበቅበታል ብለዋል።

አቶ መለስ አክለውም የአድዋ ድል ነጭ ካልሆነ በቀር ማሸነፍ አይቻለም የተባለውን አስተሳሰብ የቀየረ በመሆኑ ወጣቱ ከአባቶቹ የወረሰውን ጀግንነት፣ የእኩልነት ኃይል በመሆኑ  ከደም መልስ በሚከፈል መስዕዋትነት የሀገሪቱን ኢኮኖሚዋን ማሳደግና ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ ይገባዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የወጣቶችና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አብርሀም ታደሰ በበኩላቸው፣ የአድዋ ድል በዓል ሲከበር በዋነኛነት ድሉ የአሸናፊነት ስሜት ለትውልዱ የሚያሰርፅ ነው።

ስለሆነም የዛሬው የአድዋ ድል የሚጠይቀው መሳሪያ ይዞ መዋጋት ሳይሆን ወጣቱ ይህችን ሀገር በለውጥ የማሻገር አደራ ተጥሎበታል ብለዋል።

(በዙፋን አምባቸው)