አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 19/2008(ዋኢማ)- ባለፈው የበጀት ዓመት በባህላዊ የማዕድን አምራቾችና በኩባንያዎች አማካኝነት የተመረቱ የተለየዩ የማዕድናት ውጤቶች ወደ ውጭ በመላክ 309 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ ።
በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ባጫ ፋጂ ለዋልታ እንደገለጹት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በኩባንያዎችና በባህላዊ አምራቾች አማካኝነት በአጠቃላይ 8ሺ577 ኪሎግራም ወርቅ ፣ 8ሺ 485 ኪሎግራም ኦፓል፣ 729 ሺ936 ኪ.ግ የተለያዩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ፣ 328.90 ሜትር ኩብ ዕብነበረድና 190.48 ቶን ታንታለም ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ 309 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሊገኝ ችሏል ።
ከማዕድን ምርቶች አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 138 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው የተገኘው በዘመናዊ መንገድ ማዕድን ከሚያመርቱ ኩባንያዎች ሲሆን 171 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ከባህላዊ አምራቾች መሆኑን አቶ ባጫ ገልጸዋል ።
በበጀት ዓመቱ በኩባንያዎችና በባህላዊ ማዕድን አምራቾች አማካኝነት 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ሲሠራ እንደቆየ ያብራሩት አቶ ባጫ ከዕቅዱ 61 በመቶ የሚሆነው ገቢ ብቻ ተገኝቷል ብለዋል ።
ከዓለም የወርቅ የመግዛት ፍላጎት መቀነስ ጋር በተያያዘ ከወርቅ ምርት የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማካካስ የተለያዩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን በመላክ በዘንድሮ የበጀት ዓመት ከማዕድን ዘርፉ የተሻለ ገቢ ለማግኘት ጥረት መደረጉን አቶ ባጫ አመልክተዋል ።
በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ 885 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በበጀት ዓመቱ እንዲደራጁና የባህላዊ የወርቅና ሌሎች ማዕድናት ማምረት ሥራዎች ላይ እንዲሠማሩ በማድረግ 137 ሺ 697 የሥራ አጥ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ በበጀት ዓመቱ 738 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው 92ሺ 907 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን አቶ ባጫ አብራርተዋል ።
የማዕድን ፤ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የአገሪቱ ማዕድን ላኪዎች ከገዥዎቻቸው ጋር የተጠናከረ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩና ትውውቅ እንዲያደርጉ ለማስቻል በበጀት ዓመቱ ጥረት ማድረጉን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ።