ኮምቦልቻ ፤ ሐምሌ 20/2008(ዋኢማ)– በመግንባት ላይ የሚገኘው የአዋሽ – ኮምቦልቻ -ወልዲያ (ሐራ ገበያ) የባቡር ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ አፈጻጻም 45 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ።
የአዋሽ -ኮምቦልቻ-ወልዲያ(ሐራ ገበያ) የባቡር ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አብዱል ከሪም መሐመድ የፕሮጀክቱን የግንባታ ደረጃን ለዲያስፖራ አበላት ባስጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት ነሐሴ 2006 ዓም ግንባታው የተጀመረው ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት 45 በመቶ የግንባታ ሥራው ተጠናቋል ብለዋል ።
የፕሮጀክቱን የግንባታ ሥራ ሙሉ ለሙሉ እስከ 2010 ዓም መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ በአሁኑ ወቅት የግንባታው ሥራ 24 ሰዓት እየተከናወነ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አመልክተዋል ።
የአዋሽ-ኮምቦልቻ -ወልዲያ( ሐራ ገበያ) የባቡር መሥመር በአጠቃላይ 391 ኪሎሜትር ርቀት የሚሸፍን መሆኑን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ የባቡር መሥመሩ ለመንገደኞችና ለእቃ ማጓጓዣነት አገልግሎት የሚሠጥ መሆኑን ተናግረዋል ።
የባቡሩ መሥመሩ የአዋሽ ፣ሐይቅ፤ ሰንበቴ፤ ካራ ቆሬ፣ ኮምቦልቻና የመርሳ ከተሞችን የሚያገናኝ በመሆኑ ለአካባቢው ለንግድ ልውውጥና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር እንደሆነ የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ የባቡር መሥመር ግንባታው ሲጠናቀቅ በሰዓት 120 ኪሎሜትር ያህል ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ።
የአዋሽ – ኮምቦልቻ-ወልዲያ( ሐራ ገበያ) የባቡር ፕሮጀክት በአጠቃላይ በ 1ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያፒ መርክዚ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ በተባለ የቱርክ ተቋራጭ ኩባንያ እየተገነባ እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።
በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 3ሺ500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ።