የሐረሪ ክልል ለ2009 ከ1ነጥብ8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ሐምሌ 26/2008 (ዋኢማ)-የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ለ2009 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በማፅደቅ ተጠናቀቀ። 

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ አብዱማሊክ በከር በክልሉ በ2008 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት በአብዛኛው የተሻለ አፈጻጸም የታየባቸው ናቸው ብለዋል።

11ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች በዓልን በክልሉ ለማክበር በመንግስትና በግል ባለሃብቶች የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑንም ምክር ቤቱ በጥንካሬ ገምግሞታል።

የሐረር ከተማ ከበዓሉ አስተናጋጅነቷ በተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻ መሆኗን ታሳቢ በማድረግ የከተማዋን ውበትና ፅዳት ለመጠበቅ በህብረተሰቡ የተሠሩ ሥራዎችም በምክር ቤቱ አድናቆት ተችሮታል ነው ያሉት አፈ ጉባኤው።

በጉባኤው መጨረሻም የምክር ቤቱ አባላት የተራቆቱ ቦታዎችን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ የችግኝ ተከላ ማካሄዳቸውን፥ የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።(ኤፍ ቢ ሲ)