ባለሥልጣኑ በ2008 በጀት ዓመት 1ሺ412 ኪሎ ሜትር መንገድ መገንባቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 19/2008(ዋኢማ)- የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 2008 በጀት ዓመት 1ሺ412 ኪሎ ሜትር መንገድ  መገንባቱን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 1ሺ557 ኪሎ ሜትር መንገድ ደረጃ  ለማሻሻል፤ ለማሳደግና ለመገንባት አቅዶ የ1ሺ412 ኪሎ ሜትሩን ግንባታ ማከናወኑን ለዋልታ ገልጿል፡፡ በዚህም የእቅዱን 93 በመቶ መፈፀሙን ነው ያመለከተው፡፡

ወቅታዊ፣ ከባድና መደበኛ ጥገናን ጨምሮ የ20ሺ690 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራ ለማከናወን ታቅዶ የ19ሺ311ኪሎ ሜትር የክንውን አፈፃፀም መመዝገቡን የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለዋልታ ገልፀዋል፡፡

አቶ ሳምሶን እንደሚሉት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ 23 ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 28 የዋናና አገናኝ መንገዶች፣ 52 የጥገና ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል የኮንትራት ውል ስምምነት ከሀገር በቀልና የውጭ ሥራ ተቋራጮች ጋር ተፈፅሟል፡፡

አብዛኛው ሥራ በሀገር በቀል ሥራ ተቋራጮች መያዙን ዳይሬክተሩ ጠቁመው መንግስት የሀገር በቀል ሥራ ተቋራጮችን ተሳትፎ ለማሳደግ የያዘው አቅጣጫ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡ በበጀትመቱ ለተከናወኑት ተግባራት 25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፡፡

ለዕቅድ አፈፃፀሙ ምሉዕ አለመሆን የሥራ ተቋራጮች አቅም ማነስን ተከትሎ ግንባታቸው የተቋረጡ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን አቶ ሳምሶን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ደካማ አፈፃፀም የተመዘገበባቸው የሐዋሳጭኮ እና ጭኮይርጋጨፌ መንገዶች ግንባታን ጨምሮ የአምስት ፕሮጀክቶች ግንባታ እንዲቋረጥ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ሥራ ተቋራጮች በመምረጥ ሥራውን አፋጥኖ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የበጀት ዓመቱ አጠቃላይ አፈፃፀም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረው በተወሰኑ የመንገድ ፕሮጀክቶች የተስተዋለው መዘግየት በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለማስወገድ ይሰራል ብለዋል፡፡

ለዚህም የፕሮጀክት አፈፃፀም ክትትል ሥርዓት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሳምሶን ጠቁመዋል፡፡ ለለውጥ ሥራ እና ለመልካም አስተዳደርም ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን ነው ያመለከቱት፡፡

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የአገሪቱን የመንገድ አውታር አሁን ከደረሰበት 110ሺ ኪሎ ሜትር ወደ 220 ሺ ኪሎ ሜትር ለማሳደግ ግብ ተቀምጧል፡፡