ሚኒስቴሩ የደረጃ መሥፈርት ሳያሟሉ የተገኙ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወሰደ

አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርት ሳያሟሉ የተገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸውን ምርቶች  የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ናቸው፡፡

በ2010 በጀት አመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መሥፈርት የወጣላቸውን ምርቶች የሚያመርቱ 204 ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን ቁጥጥር ከተደረገባቸው ውስጥም የ16 ፋብሪካዎች ምርት ከደረጃ በታች ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ምርታቸው ከደረጃ በታች ሆኖ ከተገኙት ውስጥ 9 ፋብሪካዎች ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን 7 ፋብሪካዎች ደግሞ ታግደዋል፡፡

በቀጣይም ከህብረተሰብ ጤናና ከአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የምርት ጥራት ቁጥጥር በከፍተኛ ትኩረት ይሰራልም ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዋልታ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡