ከኢንዱስትሪ ምርቶች የወጪ ንግድ ከ61 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል

ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከስልሳ አንድ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት አቶ  ተካ  ገብረየሱስ  እንደገለጹት አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሆኑት የሐዋሳ ፣ኮምቦልቻና መቐለ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተመረቱ የጨርቃጨርቅ ፣ አልባሳትና የቆዳ ውጤቶችን ወደ የተለያዩ የውጭ አገራት በመላክ ነው  61 ነጥብ 1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የተገኘው ።  

በሦስቱም አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የገቡት የውጭ አገር ባለሃብቶች  በራሳቸው ወጪ ተጨማሪ የመሥሪያ ቦታዎችን ወይም ሼዶችን  እየገነቡ ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል አቶ ተካ ፡፡

ኢትዮጵያ  በተለያዩ  ክልሎች  የኢንዱስትሪ ፓርኮችን  በማስፋፋት  የወጪ ንግዷን ለማሳደግ ከመቼውም ጊዜ በላይ  ለማሳደግ እየሠራች ትገኛለች ።