የኦሮሚያ ክልል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ባዛር ዛሬ ይከፈታል

የኦሮሚያ ክልል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ትርዒትና  ባዛር ዛሬ በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ይከፈታል፡፡

በባዛሩ ላይ ከመላው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተውጣጡና የተመረጡ ሰባ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊዎች እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

በክልሉ የስራ እድል ፈጠራና የከተማ ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ እንደገለጸው የንግድ ትርዒትና ባዛሩ ከዛሬ ሚያዚያ 22 ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ይቆያል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የሚጫወቱት ጉልህ ድርሻ  እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በዚህ የንግድ ትርዒትና ባዛር ላይ በክልሉ ከሚገኙ አጠቃላይ ኢንተርፕራይዞች ውስጥ ከ 1 ሺህ በላይ ለሚሆኑት የሽግግር እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡