ሻንግቴክስ የተባለ የቻይና ጨርቃጨርቅ ኩባንያ አዲስ ቅርንጫፍ በዱከም አስመረቀ

ሻንግቴኬስ የተባለ ግዙፍ የቻይና የጨርቃጨርቅ ኩባንያ አዲስ ቅርንጫፍ በዱከም ኢንዱስትሪ ዞን አስመረቀ ።

ኩባንያው ሎንቶ ጋርሜንት የተባለውን ቅርንጫፍ የከፈተ ሲሆን ሥራውን ለመጀመር የሚያስችሉትን የተለያዩ ማሽነሪዎችንና ሌሎች ግብዓቶችን ወደ ኢንዱስትሪ ዞኑ ማስገባቱን ገልጿል። 

ኩባንያው በአካባቢው ለሚገኙ 500 ያህል ነዋሪዎችም የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፥ ሙሉ በሙሉ አቅሙን በመጠቀም ወደ ሥራ ሲገባም ለ1 ሺህ ነዋሪዎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ኩባንያው በኢትየጵያ ሥራውን መጀምሩ በኢትዮጵያ የሚመረቱ ምርቶች የዓለም ገበያን እንዲቀላቀሉ፣የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር እና የውጭ ምንዛሪ ለሀገሪቱ በማስገኘት ሚናው የጎላ ነው ተብሏል።(ኢዜአ)