ዓለምአቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽንና የብሔራዊ ባንክ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማበረታት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ዓለምአቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማበረታት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙ ተገለጸ ፡፡

ተቋማቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ገንዘቡም በየዓመቱ የሚያድግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ በዋናነት በዓለም አቀፍ ንግድ የፋይናንስ አቅርቦትና የውጭ ምንዛሬ ዋስትና እና በሀገር ውስጥ የግል ባለሀብቶች በብር ደረጃ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ነውም ተብሏል፡፡

አለምዓቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይ ኤፍ ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት ለግል  ኢንቨስትመንት  ድጋፍ  የሚውል የ452 ሚሊዮን ዶላር  ድጋፍ አድርጓዋል፡፡

ስምምነቱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ከአይ ኤፍ ሲ ተወካይ ጋር የተፈራረሙት ሲሆን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴና የአይ ኤፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሌሆር ፕሊፍ ተገኝተዋል፡፡