ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ስምምነቶችን ተፈራሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7/ 2007 (ዋኢማ) – የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለሶስት ቀናት ለጉብኝት አልጄሪያ መገኘታቸው ተከትሎ ሁለቱ አገራት በተለያዩ ዘርፎች ስምምነቶችን ተፈራርሙ።

ከስምምነቱ መካከል በዲፕሎማሲ እና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ይገኝበታል።

በተጨማሪም በእንስሳት ጤና እና በባለሙዎች ስልጠና ላይ ያተኮረ ስምምነትም በሁለቱ አገራት መካከል ተፈርሟላ።

የፊርማ ስነ ስርዓቱ የተከናወነው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደልማሌክ ሴላል በተገኙበት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም በአልጄሪያ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረገ አገሪቱ የገቡት ቅዳም ከሰዓት በኋላ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደልማሌክ ሴላል ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አቶ ኃይለማርያም አልጄሪያን ከቅኝ ገዢዎች ነፃ ለማውጣት በተደረገው ትግል ወቅት ለተሰዉ ዜጎች በተገነባው የመታሰቢያ ሀውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በተጨማሪም የአገሪቱን ብሄራዊ ሙዚም ጎብኝተዋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)