የአሸጎዳ የነፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት ዛሬ በሙከራ ደረጃ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት

አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2004/ዋኢማ/ – የአሸጎዳ የነፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት ዛሬ በሙከራ ደረጃ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ይጀምራል። ፕሮጄክቱ የሙከራ ሃይል ማመንጨት ስራውን የሚጀምረው በ15 ሜጋ ዋት ነው።

የነፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጄክቱ በ2005 ሲጠናቀቅ 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።

ፕሮጄክቱ በ210 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ እየተካሄደ መሆኑንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ ተናግረዋል።

ፕሮጄክቱ ለ300 ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን 50 ያህል የውጭ ዜጎችም በስራው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።