በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከ720 ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ከወባ ወረርሽኝ መታደግ መቻሉ ተገለፀ

ሐረር ጥቅምት 11/2004/ዋኢማ/ – በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል በተካሄደ የጸረ-ወባ መድሀኒት ርጭት ከ720ሺ የሚበልጡ ነዋሪዎችን ከወረርሽኙ ለመታደግ መቻሉን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሐንጋቱ መሀመድ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለጹት፤ ነዋሪዎቹን ከወባ በሽታ ለመጠበቅ የተቻለው በዞኑ 19 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 56 ወባማ ቀበሌዎች በተደረገ የመድሀኒት ርጭት ነው፡፡

በርጭቱ ከ206ሺ 738 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 28ሺ 800 ኪሎ ግራም ዴልታ ሜትሪን የተባለ ጸረ-ተባይ ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉን ወይዘሮ ሀንጋቱ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በወረዳዎቹ 252 የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ 720 ሺ 292 ነዋሪዎችን ለመጪዎቹ ስድስት ወራት ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ለመከላከልና ለመጠበቅ እንደሚያስችል አመልክተዋል፡፡

ከመድሀኒት ርጭቱ በተጨማሪ 357ሺ 454 በኬሚካል የተነከረ የአልጋ አጎበር ለዘጠኝ ወረዳዎች መከፋፈሉንም ምክትል መምሪያ ኃላፊዋ ማስረዳታቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡