አስተዳደሩ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችቱን ወደ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ከፍ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ ጥቅምት 20/2004/ዋኢማ/ – የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር 410 ሺ ሜትሪክ ቶን የነበረውን የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ወደ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ከፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ዝግጅት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ። በሩብ የበጀት ዓመቱም ከ90ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል በብድር ሰጥቷል።

የአስተዳደሩ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ግዛው አብቴ ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ አስተዳደሩ ክምችቱን ወደ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ከፍ ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የመጋዘን ቦታ መረጣና ጥናት አጠናቋል።

በቅርቡም የመጋዘን ግንባታ ስራ እንደሚጀመር የገለፁት አቶ ግዛው፤ የሱዳንና የቱርክ የእህል ክምችት አያያዝና አጠቃቀም ምን እንደሚመስልም የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የተመረጡ ቡድኖች በየሀገራቱ ያለውን የመንግስትና የግል የእህል ማከማቻ መጋዘኖችን ተሞክሮ ማየት መቻሉንም ጠቁመዋል።

አስተዳደሩን የክምችት አቅሙን ከፍ ለማድረግ ያቀደው የአምስት ዓመቱን የትራንስፎርሜሽን እቅድ ከማሳካት አንፃር ነውም ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በአስተዳደሩ ያለው የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ለስድስት ሚሊየን ህዝብ ለስድስት ወራት መመገብ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው፤ ወደ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ከፍ ሲደረግ ግን የሀገሪቱን ግማሽ ህዝብ ማለትም 40 ሚሊየን የሚሆነውን ለተከታታይ ስድስት ወራት የመመገብ አቅም ይፈጥርለታል ብለዋል።

አስተዳደሩ በሩብ የበጀት ዓመቱ 36 ሺ ሜትሪክ ቶን እህል ለዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ 42 ሺ 703 ሜትሪክ ቶን ለገበያ ዋጋ ማረጋጊያና 11ሺ 605 ሜትሪክ ቶን ደግሞ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል እህል በብድር መስጠቱን አቶ ግዛው ተናግረዋል።

እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ከአስተዳደሩ ብድር የወሰዱት የዓለም ምግብ ፕሮግራም 22ሺ 353 ሜትሪክ ቶንና የግብርና ሚኒስቴር ከአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ 11 ሺ 601 ሜትሪክ ቶን እህል ተመላሽ ማድረጉን ተናግረዋል።

በክምችት ተይዞ ያለው እህልም ለብክነትና ለብልሽት እንዳይጋለጥ አስተዳደሩ ተገቢውን እንክብካቤ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ338 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል በያዙ መጋዘኖች ግድግዳ፣ ጣሪያ፣ ወለልና የእህል ድርድር ላይ የተባዮችን ክስተት ለመከላከል የፀረ-ተባይ መድሃኒት ርጭት ተካሂዷል ብለዋል።

አስተዳደሩ ከሚይዘው የምግብ ክምችት በተጨማሪም በአስቸኳይ አደጋዎች ወቅታዊ ዕርዳታ ለማድረግ የሚያስችሉ ምግብ ነክ ያልሆኑ የመጠባበቂያ ቁሳቁሶችን በክምችት እንደሚይዝ ጠቁመው፤ ከተበዳሪዎች በኩል ግን ጥያቄ እንደማይቀርብ ተናግረዋል።

ሆኖም አስተዳደሩ 20ሺ ብርድ ልብሶች፣ ስምንት የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከሮች፣ አስር ሺ የውሃ መያዣ ጀሪካኖች፣ 600 ጥቅል የመጠለያ ፕላስቲክ ሽቶች፣ ስድስት ጄኔሬተሮችና አራት የውኃ ማጣሪያዎች በክምችት ይገኛል።

የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር በ1965 እና በ1966 ዓ.ም በሀገሪቱ ተከስቶ በነበረውና የብዙ ኢትዮጵያውያንና እንስሳት ሕይወት ሰለባ ባደረገው ርሃብ መንስኤነት  በ1974 ዓ.ም የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሰጠው 12ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ መነሻነት በፕሮጀክት መልክ በእርዳታ ማስተባበሪያና መቋቋሚያ ኮሚሽን ስራውን መጀመሩ የሚታወስ መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።