የጥምቀት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 11/2006 (ዋኢማ) – በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ሲከበር በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከውጭ የመጡ ጎብኝዋች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ለሐገሪቱ ሠላም እና ልማት ምዕመኑ የበኩን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪያቸውን አስተላልፍዋል፡፡

ብጹዕነታቸው በሐገራችን የሚካሄደው ልማት፣ እድገት እና ብልጽግና ግቡን እንዲመታ ለማድረግ ቤተ-ክርስደቲያን እና አባሎቿ የሚገባቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

ብጹዕነታቸው በማከልም የሐገር ልማት የቤተ-ክርስቲያንም የወገንም የሁችንም ልማት እና እድገት በመሆኑ   ሁላችንም በየተሰማራንበት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለበን በማለት ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከልማቱ ጎን ለጎን ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ያለበት ጉዳይ የሠላምና ፍቅር ጉዳይ በመሆኑ ከሁሉም በላይ በሐገራችን ሠላም እና ፍቅር እንዲሰፍን ሁላችንም መስራት  አለብን በማለት ብጽዕነታቸው ተናግረዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የግብጽ አምባሳደር መሃመድ እንድሪስ በዓሉ መንፈስን የሚያነቃቃና ልዩ ድምቀትን የሚሰጥ ሆኖ እንዳገኙት ነው የተናገሩት፡፡

አምባሳሩ እንዳሉት ይህን በዓል አብሬ ከኢትዮጵያውያን ጋር ሆ|ኜ ሳከብር ለሶስተኛ ጊዜ በመሆኑ ትልቅ ክብር ይሰማኛል፡፡ በዚህች ታላቅ ሐገር ሶስተኛ አመቴን ይዣለሁ፡፡ በእውነት በዓሉ በየአመቱ በአዲስ መልክ የሚያነቃቃ እና ልዩ የሆነ በዓል ነው በማት ገልጸዋል፡፡

እንደ ኢሬቴድ ዘገባ ሌሎችም የበዓሉ ታዳሚዎች በኢትዮጵያ ያለውን እንዲህ አይነቱን ሥነ-ሥርዓት እና የበዓሉን ትወፊታዊነት አጠናክሮ ማስቀጠል በወጣቱ ትውልደ የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡