ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ ሸ ፣ ጥር 12/2006 (ዋኢማ) – የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያ ደሳለኝ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ምክትል ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህ ሞሃመድ ቢን ራሺድ አል ማክቶም ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
ዕሑድ ጥር 11 ቀን 2006 ዓ.ም የሁለቱ ሐገራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት እና በምስራቅ አፍሪካ ስላለው ሁኔታም ምክክር አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው  ወቅት ከዚህም ባለፍ የሁለቱን ሐገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ በኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት፣ በግብርና እና በቱሪዝም ዘርፍ በስፋት መስራት በሚቻልበት ዙሪያ ላይም ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚንሰትር ኃይለማርያመ ደሳለኝ ኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የግል ባለሃብቶችን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬት ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚንስትር ሼህ ሞሃመድ ሐገራቸው ከወንድማማች እና እህትማማች ሐገራት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለመመስረት ፋለጎቷ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ (ኢሬቴድ)