የፖሊስ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ተከበረ

ነሐሴ 17/2008(ዋኢማ)-  በኢትዮጵያ የኢፌዴሪ የፖሊስ ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ  ተከበረ።

"ህገመንግስታችንን በመጠበቅ ለህዝባችን ሠላምና ለህግ የበላይነት የማንከፍለው መስዋእትነት የለም"  በሚል መሪ ቃል ነው ቀኑ የተከበረው፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ህገ መንግስቱንና ህገ መግንስታዊ  ስርአትን ለመጠበቅ የፖሊስ ሰራዊት እያከናወነ ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ሀገራዊ አንድነትን ለመናድ የሚንቀሳቀሱ ፀረ- ሰላም ሀይሎችን ሴራ ለማክሸፍ እየፈጸመ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አሰፋ አብዩ ጠንካራ የፖሊስ ሀይል ለመገንባት የሚከናወኑ የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው  ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

እለቱ ሲከበር በግዳጅ ወቅት የተሰው አባላት ታስበዋል፡፡ መልካም አፈጻጸምን ያሳዩ የፖሊስ አባላትም ተሸልመዋል፡፡(ኢቢሲ)