የብአዴን 36ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል በድምቀት ተከበረ

የብሔረ አማራ ዲሞክራያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) የተመሰረተበት 36ተኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ፡፡

የድርጅቱ የምስረታ በዓል በባህር ዳር ሙሉ አለም አዳራሽ በተለያዩ  ዝግጅቶች በክልል ደረጃ በድምቀት ተከብሯል።

ብአዴን ያገጠመውን ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም አዝማሚያና የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

በዓሉ "በጥልቀት በመታደስ ክልላዊና አገራዊ ህዳሴያችን እናፋጥናለን" በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን የምስረታ በዓሉን በማስመልከትም የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በዚህም የብአዴን ህዝባዊ ትግል፣ የህዳሴው ጉዞና የትውልዱን ሚና የሚመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡ የድርጅቱን ሂደትና ወቅታዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ አስተያየቶች ቀርበውም ውይይት ተካሂዶባዋል፡

በምስረታ በዓሉ ላይ ከ1500 በላይ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር ፣እንዲሁም የባህርዳር ዙሪያ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞችና የባህርዳር ከተማ ወጣቶችና ሴቶች ተሳትፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ ያሉ የድርጅቱ አባላትና  ደጋፊዎችም የምስረታ በአሉን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።

ድርጅቱን የገጥሙትን ስልጣንን ለግል ጥቅም የማዋልና የመልካም አሰዳደር ችግሮችን በመፍታት በጥልቅ የመታደስ እንቅስቃሴውን እውን እንደሚያደርጉ በበዓሉ ላይ የተገኙ  የብአዴን አመራሮች ተናግረዋል።