የአማራ ክልል ምክር ቤት የካቢኔ አባላትን ሹመት አፀደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ መደበኛ ጉባዔ 22 አዳዲስና ነባር ካቢኔዎችን ሹመት አፀደቀ፡፡

ከተሿሚዎቹ መካከል 12ቱ አዳዲስ አመራሮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 10ሩ ደግሞ በያዙት ኃላፊነት የቀጠሉ ናቸው፡፡

ተሿሚዎቹ በትምህርት ደረጃቸው ፣በአገልግሎት ዘመናቸው፣ባላቸው የአመራር ብቃትና ህዝቡን የማገልገል ፍላጎት ተመዝነው ለሹመት የቀረቡ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናግረዋል፡፡

ባሉበት የቀጠሉ ነባር የካቢኔ አባላት

1. አቶ ብናልፍ አንዷለም – ምክትል ርዕሰ መስተዳደር

2. አቶ ተስፋየ ጌታቸው – የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ

3. ዶክተር ተሸመ ዋለ – ግብርና ቢሮ ሃላፊ

4. ወይዘሮ ገነት ገብረ እግዚአብሄር – ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ

5. አቶ ጃንጥራር አባይ – የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ

6. አቶ ፍርዴ ቸሩ – የፍትህ ቢሮ ሀላፊ

7. ወይዘሮ ፈንታዬ ጥበቡ – የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ

8. አቶ ገለታ ስዩም – ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ

9. አቶ ንጉሱ ጥላሁን – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ

10. አቶ በድሉ ድንገቱ – ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

አዲስ የተሾሙካቢኔ አባላት

1. ዶክተር ይልቃል ከፍ አለ አስረስ – የትምህርት ቢሮ ሀላፊ

2. ዶክተር አበባው ገበየሁ – የጤና ቢሮ ሀላፊ

3. አቶ ሞላ ፈጠነ – የውሃ መስኖ ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ

4. አቶ ጸጋ አራጌ – የመሬት አስተዳደርና ጥበቃና ቢሮ ሀላፊ

5. አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት – የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ

6. ዶክተር ጥላሁን መሀሪ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

7. ዶክተር ሂሩት ካሳው – የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

8. አቶ ሞላ ጀንበሩ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

9. አቶ መሀመድ አብዱ – የገቢዎች ባለስልጣን ዳይሬክተር

10. ዶክተር በላይነህ አየለ – የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ቢሮ ሀላፊ

11. አቶ ላቀ አያሌው – የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ሀላፊ

12. ወይዘሮ ወለላ መብራት – የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ

ምክር ቤቱ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሹመት በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጭ ድምጽ አፅድቋል። 

ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ቃለ መሃላ ፈፀመዋል፡፡