ዶክተር መራራ የአዋጁን መመሪያ በመተላለፋቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግስት አስታወቀ

ዶክተር መራራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መመሪያ ተላልፈው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግስት አረጋገጠ።

ዶክተር መራራ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ ቁጥር አንድ አንቀጽ 2 ላይ የተመለከተውን መመሪያ ተላልፈው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት አስታውቀዋል።

መመሪያ ቁጥር አንድ አንቀጽ 2 በሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶችና ከፀረ ሰላም ቡድኖች ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ማድረግ ክልክል መሆኑን ይደነግጋል ሲል ነው የገለጸው ።

ዶክተር መራራም ይህን ክልከላ በመተላለፋቸው ምክንያት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ነው ያለው ።

ሰሞኑን ዶክተር መራራ በቤልጅየም ብራሰልስ በአሸባሪነት ከተፈረጀው ግንቦት ሰባት ቡድን መሪ ብርሃኑ ነጋ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውና መግለጫ ማውጣታቸው የሚታወስ ነው-(ኤፍ ቢ ሲ) ።