ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የሐረር ከተማ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ

11ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዛሬ ሃረር ከተማ ገብተዋል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸውም ፣ በ250 ሚሊየን የተገነባው የሐረሪ የባህል ማዕከል ፣በ1 ቢሊየን ብር በመገንባት ላይ ያለው ሕይወት ፋና ተሪሼሪ ሪፈራል ሆስፒታል እና የከተማውን ህዝብ የመጠጥ ውሃ ችግርን ሙሉ በሙሉ ሊያስወገድ ይቻላል የተባለው ቃሌ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ጎብኝተዋል ፡፡

ይኸው በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው ሆስፒታሉ 1ሺ አልጋዎች ያሉትና ከክልሉ አልፎ የምስራቅ ኢትዮጵያን ህዝቦችን ለማስተናገድ እንደሚችል ነው የተመለከተው ፡፡

በዋዜማው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለማድመቅ ማንነታቸውን ለማሳወቅ የተለያዩ ትርኢቶችን በዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወር አቅርበዋል ፡፡

በነገው ዕለት በከተማው እየተገነባ ባለው ዘመናዊ ስታድየም ደግሞ 3ሺ ብሄሮች ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጨምሮ 40 ሺህ የሐረር ከተማና የአከባቢዋ ህዝቦች በተለያዩ ትርኢቶች ያደምቁታል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዋልታ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል፡፡

ኤዲተር በሪሁ ሽፈራው