ግብጽ የተለያዩ የሰው አካላት የሚያዘዋውሩ 25 ሰዎችን አሰረች

ግብጽ  በተለያዩ የሰው አካላት ዝውውር የተሰማሩ 25 ሰዎች ማሰሯን አስታወቀች ፡፡

እነዚህ ፕሮፌሰሮች ፣ዶክተሮችና ነርሶች የሚገኙባቸው ሰዎች በሰው አካላት ህገወጥ ተግባር ዝውውር ተግባር የተሰማሩ መሆናቸውን ነው የግብጽ የአስተዳር ቁጥጥር ባለስልጣን የገለጸው  ፡፡

ከነዚሁም ውስጥ ደላሎችና የሰዎች አካላት ሻጮች እንደሚገኙባቸውም  ጠቁሟል፡፡

የግብጽ ድሆች ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ኩላሊቶቻቸውን፣ሳምባቸውንና ሌሎች አካላቶቻውን እንደሚሸጡ ነው ያመለከተው ፡፡

የሚበዙት ግን ህገ ወጥ የሰው አካላት አዘዋዋሪዎች ከተለያዩ የሲናይ በረሃ ያዘዋወሩዋቸውን ስደተኞች ለአደጋው የተጋለጡ መሆናቸውን አስታውቋል ፡፡

የሰው አካላት ዝውውሩ በርካታ ህገወጥ ሰዎች የበለጸጉበት ሲሆን ለበርካታ ሰዎች ደግሞ ለከፍተኛ አለመረጋጋት የዳረገ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል ፡፡

ይህ አደጋኛ የህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች መዋቅር ለመያዝ በተደረገ ዘመቻ በሚሊየን የሚቆጠር ዶላሮችና ወርቆችን በቁጥጥር ስር መዋኑን ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው ፡፡

አሁን በቁጥጥር ስር የዋለው የወንጀለኞች ስብስብ ከፍተኛው የዓለም አቀፍ የሰው አካላት አዘዋዋሪ ቡዱን እንደሆነ የግብጽ መንግስት ማረጋገጡን ቢቢሲን  ዘግቧል ፡፡