292 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

መጋቢት 03/2013 ዓም (ዋልታ) – 292 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረብያ ጂዳ ዛሬ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።