ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም የአዋሽ -ወልድያ -ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክትን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአዋሽ ወልድያሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የጀመረው ከኮምቦልቻ የባቡር ጣቢያ ሲሆን እስከ ድልድይ 40 ድረስ የ29 ደቂቃ የደርሶ መልስ ስኬታማ የባቡር ጉዞ ተደርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵውያን ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ የቴክኖሎጂእውቀት እየወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዋሽወልድያሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት 390 ኪሎ ሜትር ርዝመትያለው ሲሆን፥ አሁን ላይ አፈጻጸሙ 57 በመቶ ደርሷል፡፡