293 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

293 ኢትዮጵያዊያን በትናንትናው ዕለት ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ተመላሾቹ ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።