በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት 5 ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የመንግስትን ሀብትና ንብረት በመመዝበር የተጠረጠሩ የስራ ሀላፊዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉን ተግባር እንደቀጠለ መንግስት ገልጿል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባገኘው መረጃ መሰረት ዛሬም አምስት በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በዚህም መሰረት፦

  1. አቶ ደሳለኝ ገብረህይወት ተፈራ /የወደብና ተርሚናል አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፋፃሚ/
  2.  አቶ ሲሳይ አባፈርዳ /የኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ/
  3. አቶ ሲራጅ አብዱላሂ / የፕላንና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት መምሪያ ሀላፊ/
  4. ቺፍ ኢንጂነር ዓለሙ አምባዬ /የሺፒንግ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ/ እና
  5.  አቶ ሳሙኤል መላኩ /የፋይናንስ ሀላፊ/ ናቸው ዛሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
  6. ኤፍ.ቢ.ሲ)