የሱዳን ፕሬዝዳንት ለጄኔራል ሳሞራ የኑስ የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ሸለሙ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ሚና እንዲጫወት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ከሱዳን ፕሬዝዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ተበረከተላቸው፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ለቀጥናው ሰላም እና መረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ጠንካራ አመራር በመስጠት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኡመር ሀሰን አልበሽር የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ሸልሟቸዋል።

የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ ከሽልማቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ላስመዘገባቸው ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የተበረከተ ነው ብለዋል።

ይህንን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ከሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር በሰላም እና ደህንነት ዘርፍ ስንቀበል ታላቅ ክብር እና ኩራት ይሰማናል። ይህ የክብር ሽልማት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በሃገር ውስጥ እንዲሁም በቀጠናው ላስመዘገባቸው ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የተበረከተ ነው፤ሲሉ ጀነራል ሳሞራ ዮኑስ ገልፀዋል።

እሳቸው የኢፌድሪ መንግስት እና የመከላከያ ሰራዊት ላላው ብቃት እና ጥራት የተቸረ አድናቆት መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ሰራዊቱ ለአከባቢው አልፎም ለዓለም ደህንነት የሚያደርገውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።

ሰላም፣ መረጋጋት እና ደህንነት በሌለበት ልማት እና ቀጣይነት ያለው እድገት አይመጣም ያሉት ጀነራል ሳሞራ የኑስ፥ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትም በሃገሪቱ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ መሰረት ለዓለም ሰላም እና ደህንነት አስተዋፅኦውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 10 ሺህ በላይ የመከላከያ ሃይል በሰላም ማስከበር ተልእኮ በማሰማራት ከአለማችን ቀዳሚ ሃገር ናት ተብሏል።

ሃገሪቱ በብቃት በታማኝነት እና በገለልተኝነት የሚወጣ ሠራዊት መገንባትዋንም ብዙዎች መስክረውላታል።

በዓለማችን መፍትሄ የማይገኝለት የግጭት ቦታ ተብሎ የሚጠራውን የአብዬ ግዛት ግጭት ለማስቆም ሁለቱም ሱዳኖች ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ መመረጥዋም ለዚህ አንድ ማሳያ መሆኑን ተነግሯል።

ሰራዊቱ አሁንም በሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዳርፉር እና ሱዳን ግዳጁን እየፈፀመ ይገኛል።(ምንጭ:ኢቢኮ)