አቶ ሳምሶን ወንድሙና በቀለ ባልቻ በነፃ ተለቀቁ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እና በቀለ ባልቻ ከተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በነፃ ተለቀቁ።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ተረኛ ምድብ የወንጀት ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ ሳምሶን ወንድሙ እና በቀለ ባልቻ በነፃ እንዲለቀቁ ትእዛዝ ያስተላለፈው።

ጠቅላይ አቃቤ ህግም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እና በቀለ ባልቻ ምርመራ መቋረጡን ለችሎቱ በጽሁፍ አቅርቧል።

በተያያዘ አቶ የኔነህ አሰፋ የተባለ ተጠርጣሪ በ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቅም ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ አሳልፏል።

በተመሳሳይ የሀይዚ አይ.አይ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ዛኪር አህመድ በ150 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ትእዛዝ ያስተላለፈ ቢሆንም፤ አቃቤ ህግ ግን ይግባኝ ጠይቆባቸዋል።

ፍርድ ቤቱም አቃቤ ህግ የይግባኙን ምክንያት በሁለት ቀን ወስጥ አንዲያቀርብ አዟል።

አቶ ዛኪር አህመድ ከተዋሱት የ500 በርሜል ሬንጅ ጋር በተያያዘ በእነ አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል የክስ መዝገብ መከሰሳቸውም ይታወሳል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)