በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል የተፈጠሩ ግጭቶች መንስኤያቸው የድንበር ወሰን ሳይሆን የአመከላከት ችግር ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

በቅርቡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተከሰቱት  ግጭቶች  መንስኤያቸው የድንበር  ወሰን ሳይሆን የተሳሳተ የአመለካከት መሆኑን   የኢፌዴሪ ጠቅላይ  ሚንስትር  አቶ ኃይለማርያም  ደሳለኝ  ተናገሩ ።

ጠቅላይ  ሚንስትር ኃይለማርያም  በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ያቀረቡትን የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድን በተመለከተ  ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በሠጡት አስተያያት እንደገለጹት በቅርቡ በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጠሩ ግጭቶች  መንስኤያቸው የድንበር ወሰን ግጭት ሳይሆን የተሳሳቱ አመለካከቶች መሆናቸውን  ተናግረዋል ።

የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች በአገሪቱ ለሚከሰቱ ለግጭቶች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይማርያም በህዝቦች መካከል መከፈፈል የሚፈጥሩ ፖለቲካ አመለካካቶችን የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎችን በጋራ ለመፍታት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች መካከል ያለው ህገ ወጥ የጫት ገበያና የውጭ ምንዛሪ ንግድ ሌላው ለከፍተኛ ግጭትና ያለመረጋጋት መንስኤ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል እንደሚጠቀሱ ናቸው ያሉት ኃይለማርያም አንዳንድ አካላት ያለመረጋጋት በአካባቢው ሲፈጠር ህገ ወጥ ንግዱን በቀላሉ ማካሄድ እንደሚችሉ ያምናሉ ብለዋል ።

በሁለቱ ክልሎች ድንበር ወሰን አካባቢ የተከሰተውን ግጭት ችግር ለመፍታትና ሁኔታውን ለማረጋጋትም  በክልሎቹ  የሚገኙ  ወጣቶች ፣ መምህራን ፣ የአገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎችም ያደረጉትን አስተዋጽኦም የሚደነቅ ተግባር መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አመልክተዋል ።

መንግሥት ከግጭቱን ለማብረድ የሰላም ኮንፈረንሶች  እንዲካሄዱ በማድረግ የተለያዩ  የተቀናጁ እንቅስቃሴዎችን  ማድረጉን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ  ለወደፊቱም  በተለያዩ  የአገሪቱ የክልሎች ድንበር ወሰንም ሆነ አገር አቀፍ  የሆነ   የሰላም  ኮንፈረንሶችን ለማዘጋጀት  እቅድ እንዳለው  ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም አስረድተዋል ።

በተጨማሪም  መንግሥት  በሶማሌና በአሮሚያ ክልሎች  በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ  ወደ መኖሪያ  ሥፍራቸው እንዲመለሱ  ለማድረግ  በምክትል ጠቅላይ  ሚንስትር የሚመራ  ኮሚቴ  አዋቅሮ  የመልሶ የማቋቋም ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል ።

በሁለቱ ክልሎች ድንበር ወሰን አካባቢ በተፈጠሩ ግጭትን ለመከላከል  የመከላከያ  ሠራዊት እርምጃ አልወሰደም የሚል ጥያቄ ከምክር ቤት አባል የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ መሠጡት ምላሽ እንደገለጹት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በፍጥነት ገብቶ እርምጃ ባይወስድ ኖሮ  የደረሰው  ጉዳት  ይባባስ እንደነበር  አስረድተዋል ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በምክር ቤቱ በሠጡት አስተያያት በአገሪቱ የሚሠሩ የግልና የመንግሥት ሚዲያዎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት  የግንባታ ሥራው  የሚኖራቸው አስተዋጽኦ   ወሳኝ  በመሆኑ  መንግሥት  የሚዲያ  ሪፎርም ፕሮግራም አዘጋጅቶ እየተንቀሳቀሰ  ይገኛል ብለዋል ።

የአገሪቱ ሚዲያዎች  ለህብረሰተቡ  ወቅታዊ ፣ ትክክለኛና ተገቢ  የሆነ መረጃን   በመሥጠት በኩል ያለባቸውን ክፍተቶችን ለመሙላትም የሚዲያ ሪፎርም ፕሮግራሙ የሚዲያ ባለሙያዎች  አቅም ግንባታ ላይ የሚያተኩር መሆኑን  ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቁመዋል ።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት የማህበራዊ ሚዲያ  በአሉታዊ ሁኔታ ግጭትና ጥላቻን የሚሰብኩ መልዕክቶች እንዳይተላላፉበት በማድረግ በኩል የተጀመሩት  ዘመቻ  በመጠቀም  የማህበራዊ  ሚዲያ ለበጉ  ሥራ እንዲውል  ለማድረግ  መሥራተ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚንስትሩ  ጠቁመዋል ።

ከመንግሥት የሥራ ኃላፊነት በፈቃደኝነት ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡ አመራሮችን በተመለከተ  ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ በሠጡት ምላሽም በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚመራ  አገር የመልቀቅ ጥያቄ  መቅረቡ ሊለመድ የሚገባ  መሆኑን  ጠቁመው ከወጣትነት ጀምሮ  ኢህአዴግን ሲያገለግሉና የላቀ አስተዋጽኦ ሲያበረክቶ የቆዩት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት ጥያቄ  ተቀባይነት አግኝቷል ብሏል ።

አቶ አባዱ ገመዳ  ለመልቀቅ ያቀረቡት  ጥያቄም  በዴሞክራሲያዊ ሁኔታ ውይይት እየተደረገበት  መሆኑንና  ውይይቱ እንደተጠናቀቀ  ውጤቱ የሚታወቅ መሆኑን  ጠቅላይ ሚንስትሩ  አስገንዝበዋል ።

ገዠው ፓርቲ ኢህአዴግ ከተለያዩ  ፓርቲዎች  ጋር የሚደረገው ውይይትም የአገሪቱን  ለጋ የዴሞክራሲያዊ  ሥርዓትን በማጠናከር  በኩል  አስተዋጽኢ  የሚያደርግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ   የምርጫ  ሥርዓቱን ጨምሮ በአንዳንድ ጉዳዮች  ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል ።