ሱዳን የአገሪቱን የተፈጥሮ ሃብትን ለኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ መሥራት እንደሚገባት ተመለከተ

ሱዳን የአገሪቱን የተፈጥሮ ሃብት ለኢኮኖሚ እድገቱ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማሳደግ  እንደሚገባት  የሱዳን  ንግድ  ሚኒስቴር አስታወቀ ።

በአሜሪካ ለሁለት አስርት አመታት ተጥሎ የነበረው የኢኮኖሚ ማዕቀብ መነሳቱ ኢኮኖሚ ማንሰራራት  እድል ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡

የሱዳኑ የንግድ ሚንስትር ሀቲም አል ሲር ሀገራችን ኢኮኖሚዋ እንዲያድግ ከተፈለገ የሚያስፈልገን የተፈጥሮ ሀብቷን ልትጠቀም ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ አመታት የኢኮኖሚውን ማዕቀብ መነሳት ተከትሎ ከሀገራት ጋር ያለን ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለለውጥ እንጠቀመው ብለዋል፡፡

የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ ኮሜሳ በሱዳን ካርቱም አዘጋጅቶት በነበረው  አውደጥናት ላይ የተገኙት ሚንስትሩ አሁን የተለያዩ አለም ላይ ያሉ ኢንቨስተሮች በሱዳን ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎቱ እያሳዩ ስለመሆናቸው ተረድተናል ብለዋል፡፡

የኢንቨስተሮች ፍላጎት ለሀገሪቱም ለኢንቨስተሮችም ጥቅም ለማዋል ይሠራል ሲሉም አስታውቀዋል፡፡

 በተለይም ከምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ ኮሜሳ አባል ሀገራት ጋር ያላቸውን የንግድ ልውውጥ መጠን ከፍ ለማድረግ  ተዘጋጅተናል ነው ያሉት የሱዳኑ የንግድ ሚንስትር ሀቲም አል ሲር፡፡

የጋራ ገበያው ሱዳን ማዕቀብ ውስጥ ሁናም ከዛ በኋላ ባለው ጊዜ ከሱዳን ጎን መቆሙ ምስጋና ይገባዋል በማለት አሞካሽተውታል፡፡

ሱዳን በተጣለባት ማዕቀብ የተነሳ ኢኮኖሚዋ እጅግ ስለመጎዳቱ አሀገራት ጋር የነበራት ግንኙነት ስለመበላሸቱ ለኮሜሳ አውደ ጥናት ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡ በዚህ ሁላ ጫና ውስጥም ቆይታ ከቀጠናው ከሌሎች አለም ሀገራት ጋር የውጭ ግንኙነቷ እንዳይስተጓገል እየሰራን ቆይተናል ሲሉ የሀገሪቱን የጫና መቋቋም አሳይተዋል፡፡

ሚንስትር ሀቲም አል ሲር የቀጠናው ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት የተጠናከረ እንዲሆን ባወጣው የድርጊት መራሀ ግብር አውጥታ እየሰራች ስለመሆኑ አስታውቀዋል፡፡

የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ ኮሜሳ አላማ የተሳካ እንዲሆን ቁርተኝነቷን እያሳየችም ነው ብለዋል፡፡ ሱዳን በአሜሪካ ተጥሎባት የቆየውን ማዕቀብ የተነሳላት በሰብአዊ መብት አያያዝ መሻሻል ማሳየቷ መረጋገጡን ተከትሎ ነው፡፡

ማዕቀቡ የተጣለው እ.እ.አ 1997 ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አሜሪካ በወቅቱ ሱዳን ሽብርተኝነትን ትረዳለች በማለቷ ነው፡፡ የአልቃኢዳው መሪ ኦሳማ ቢላደን ካርቱም እንዲኖር በመፍቀዷ አሜሪካን ለኢኮኖሚ ማዕቀቡ እደገፋፋት ዳራው ያሳያል፡፡

ከተነሳ ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው የኢኮኖሚ ማዕቀብ መሠረታዊ ለሆኑ የሰብአዊ መብቶች መሻሻል ፤ሙስናን ለመከላከል ፤ሰላም የራቃቸው የተለያዩ የሱዳን አከባቢዎች ሰላም እንዲያገኙና መሰል በርካታ  ውጤቶች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኦል አፍሪካን ነው የዘገበው፡፡