ኢትዮጵያና ኳታር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት አደረጉ

ኢትዮጵያና ኳታር ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሏቸው የተለያዩ ጉዳዮች  ላይ ስምምነት አደረጉ             

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሀማድ አልታኒ ጋር የሁለቱ አገራት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ጋር  ውይይት አድርገዋል ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ከኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሀማድ አልታኒ ጋር በተለያዩ  የጋራ  ጉዳዮች  ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ በኢንቨስትመንትና በንግድ  ትብብር  ለማድረግ ስምምነት ፈጽመዋል።            

በኳታሩ አሚር በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኳታር ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ  ተባብራ ለመሥራት  ፍላጎት እንዳለት ገልጸዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ በመሆኑ በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት እና የንግድ እድሎች መጠቀም ትፈልጋለች ብለዋል፡፡  

አሚሩ፣ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ለምታደርገው አስተዋጽኦ ኳታር ታላቅ አክብሮት እንዳላት ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አጋር ናት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለምትከተለው በመርህ ላይ የተመሰረተው ፓሊሲዋ አገራቸው ከበሬታ ያላት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ለምታደርገው የልማት እንቅስቃሴ ኳታር ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከውይይቱ ቀደም ብሎ የኳታርን ፋውንዴሽንን  ጎብኝተዋል፡፡