ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከሱዳን መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹምን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም የሆኑትን ሌተናል ጀነራል ኢማድ አልዲን አዳዊን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ኢታማዦር ሹሙ ከፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የተላከን መልዕክት አድርሰዋል።

በውይይቱም የሁለቱ አገራት ስትራቴጂያዊ ትብብርን በሚመለከቱ ሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ፣ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።