በሚያወጡት ከፍተኛ ድምጽ ሳቢያ በናይሮቢ ሁለት የምሽት ክለበች ተዘጉ

ሁለቱ ስመጥር የምሽት ክለቦች ከነዋሪዎች በቀረበባቸው ቅሬታ ምክንያት ነው የናይሮቢ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት እንዲዘጉ ያደረገው፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እንደገለጸው  በርካታ ቁጥር ያላቸውና በምሽት ክለቦቹ አቅራቢያ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪች ከክለቦቹ የሚወጣውን እጅግ ከፍተኛ ድምጽ መቋቋም እንደከበዳቸው ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

ከነዋሪዎቹ ቅሬታ በመነሳት የከተማው ባለስልጣናትና ፖሊስ በጋራ በመሆን ስፔስ ላውንጅ እና ግሪል ኤንድ ቢ የተባሉት እነዚህ የምሽት ክለቦች እንዲዘጉ አድርገዋል፡፡

ክለቦቹ የሚያወጡትን ከፍተኛ ድምጽ እንዲቀንሱ ከከተማ አስተዳደሩ በተደጋጋሚ ቢጠያቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውም ተነግሯል፡፡

ክለቦቹ የተለያዩ ታላላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሚካሄዱባቸው ነበሩ ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡