ምክር ቤቱ የካቢኔ አባላትን ሹመት ዛሬ አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በነበረው መደበኛ ስብሰባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ያቀረቡዋቸውን 16 እጩ የካቢኔ አባላት ሹመት አጸደቀ ፡፡

የኢፌዴሪ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ 1084/2010 ረቂቅ አዋጅን በሶስት ተቃውሞና በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጸደቀ ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሴቶችን ተሳትፎ ማስፋት የሚያስፈልግ መሆኑን በመግለጽ፤ 6 ሚኒስትሮች ካሉበት ወደሌላ እንዲሰሩ 10 አዲስ ሆነው እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ አዲሶቹ ተሿሚዎች የሚያሳዩዋቸው ጉድለቶች በምንም መልኩ የማይታለፉ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡

እነዚህም የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና ሙስናን መከላከል ብቻ ሳይሆን ገንዘብ፣ንብረትና ጊዜ ብክነትን የማስቀረት ግዴታ ያለባቸው መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አዲስ የካቢኔ አባላት እንደሚከተለው ቀርበው በምክርቤቱ ተቀባይነት በማግኘታቸው ቃለ መሓላ ፈፅመዋል ፡፡

1ኛ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የግብርናና እንስሳት ሃብት ሚኒስቴር

2ኛ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የትራንስፖርት ሚኒስትር

3ኛ ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

4ኛ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የመንግስት ልማት ድርጅት ሚኒስትር

5ኛ አቶ ዑመር ሐሰን በሚኒስቴር ማዕረግ የገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

6ኛ ወይዘሮ ኡባ መሐመድ ሁሴን የመገናኛና ኢንፎርሜን ቴክኖሎጂና ሚኒስትር

7 ኛ ዶክተር አምባቸው መኮንን የኢንዳስትሪ ሚኒስትር

8ኛ  አቶ መቱማ መቃሳ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር

9ኛ ወይዘሮ ፎዚያ አሚን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

10ኛ አቶ አሕመድ ሸዴ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

11ኛ አቶ ጃንጥራር አባይ የከተማ ልማትና ቤቶች ልማት ሚኒስትር

12ኛ አቶ መለሰ አለሙ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር

13ኛ አቶ ብርሃኑ ጸጋየ አበራ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ

14ኛ ወይዘሮ ያለም ጸጋይ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስትር

15ኛ አቶ መላኩ አለበል አዲስ የንግድ ሚኒስትር

16ኛ ዶክተር አሚር አማን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር